የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውስጥ ካሉ ክልላዊ መንግሥታት አንዱ ነው። ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት በስተቀር የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥታት ጋር ይዋሰናል። ክልሉ በምዕራብ ከሱዳን (66 ኪ.ሜ) እና በደቡብ ከኬንያ (521 ኪ.ሜ) ጋር ዓለም አቀፍ ድንበር ይጋራል። ኦሮሚያ በሕዝብ ብዛት ከፍተኛ ከሆኑት ክልላዊ መንግሥታት አንዱ ሲሆን በሀገሪቱ እምብርት ላይ ይገኛል። የክልሉ ዋና ከተማ ፊንፊኔ (አዲስ አበባ) ስትሆን እርሷም የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ናት።
የኦሮሚያ አጭር መረጃ
Seen-duubee Oromiyaa — a short official note on the regional state.