የጽ/ቤቱ ተልዕኮ ለፕሬዚዳንቱ በክልሉ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 57፣ እንዲሁም ለአስተዳደር ምክር ቤቱ (ካቢኔ) በአንቀጽ 55 የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት እንዲፈጸሙ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እና የቴክኒክና የሙያ ድጋፍ በመስጠት ብቃት ያለው አስተዳደር እንዲኖር ማድረግ ነው። በተጨማሪም የክልሉን መንግሥት አስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 162/2003 የጽ/ቤቱ ሚና እንደገና በመታወጁ ለጽ/ቤቱ ከፍተኛ ሥልጣን ተሰጥቶታል።
የጽ/ቤቱ አመሰራረት
የፕሬዚዳንት ጽ/ቤቱ መቼ እንደተቋቋመ በግልጽ የሚገልጽ ሰነድ ባይኖርም፣ የጽ/ቤቱ መቋቋም ከክልሉ መንግሥት መቋቋም ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑንና በነሐሴ (Hagayya) 1984 ዓ.ም. መሆኑን የተለያዩ ማስረጃዎች ያሳያሉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የተቋቋመው ፕሬዚዳንቱና የክልሉ መንግሥት አስተዳደር ምክር ቤት (ካቢኔ) በሕገ መንግሥቱ የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተግባር ማከናወን እንዲችሉ ለመደገፍ ነው።
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ተልዕኮ
ስለ እኛ
የዕቅድና የአደረጃጀት ሚና
ጽ/ቤቱ የአምስት ዓመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ሥራዎች አስተማማኝ በሆነ መንገድ በመፈጸምና በማስፈጸም ረገድ ከእርሱ የሚጠበቀውን የአመራር ሚና በብቃት በመወጣት ለፕሬዚዳንቱና ለካቢኔው አስተማማኝ ድጋፍ መስጠት ይኖርበታል። ከዚህ ጋር በተያያዘም በአዋጅ ቁጥር 162/2003 አንቀጽ 14 የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ለማከናወን አስፈላጊውን አሠራርና መዋቅር መዘርጋት በማስፈለጉ፣ እንዲሁም ጽ/ቤቱ ለረጅም ጊዜ የቆየባቸውን የአሠራርና የአቅም ክፍተቶች ከመሠረቱ በመፍታት ለተቋቋመበት ዓላማ በብቃት የሚሠራ ተቋም እንዲሆን የአደረጃጀት ማሻሻያ ጥናት ተካሂዷል።